በኢፌድሪ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ስር የሚገኘው የነጌሌ ቦረና መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ፅ/ቤት 45(አርባ አምስት) እና ከዚያ በላይ ሰው መያዝ የሚችል አንድ(1) የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ለሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚሆን ለ 1 /አንድ/ ዓመት ኮንትራት አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
የሠራተኛ ሰርቪስ መኪና ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያው
በኢፌድሪ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ስር የሚገኘው የነጌሌ ቦረና መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ፅ/ቤት 45(አርባ አምስት) እና ከዚያ በላይ ሰው መያዝ የሚችል አንድ(1) የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ለሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚሆን ለ 1 /አንድ/ ዓመት ኮንትራት አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ከላይ በተገለፀው መሠረት ጨረታውን መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች:-
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው /ያላት፣
- የዘመኑን የስራ ግብር የከፈለ/ የከፈለች።
- የተ.እ.ታ(ቲ.ኦ.ቲ) ተመዝጋቢ የሆነ የሆነች እና የግብር መለያ ቁጥር ያለው/ያላት።
- ኦርጅናል ሊብሬ ከእነ ኮፒው ማቅረብ የሚችል / የምትችል።
- የታደሰ የዓመቱን ቦሎ የለጠፈ እና 3ኛ ወገን ያለው/ያላት።
- ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ መኪናውን በማቅረብ በባለሙያ ለማስፈተሽ ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች።
- የድርጅቱን ሠራተኞች ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ በመንግስት የስራ ሠዓት መውጫና መግቢያ ሰርቪስ መስጠት፣ በቀን 4 ምልልስ ይሆናል::
- የኪራይ ሁኔታ ለ 1 (አንድ) ዓመት ነው፣፣
- ከላይ የተጠቀሱትን ህጋዊ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችል/የምትችል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት (15) ቀናት ጨረታው አየር ላይ የሚውል ስለሆነ መሳተፍ ይቻላል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመውሰድ የመወዳደሪያ ዋጋ ሞልታችሁ በታሸገ ፖስታ (ኤንቨሎፕ) እስከ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ ዶሎ በር ኬላ አጠገብ በሚገኘው መ/ቤታችን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት አስተዳደር ከፍል ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን አውቃችሁ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት በኋላ ጨረታው ዝግ ተደርጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማግስቱ ማለትም መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ
ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ማቅረብ የማይችሉ ተጫራቾች ዝቅተኛ የመጫረቻ ዋጋ ቢያቀርቡም በጨረታው መመሪያ መሠረት አሸናፊ መሆን የማይችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0464451707/0988080497 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡- የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ነጌሌ-ቦረና ቅርንጫፍ 03 ቀበሌ ዶሎበር ኬላ መውጫ አጠገብ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት
