በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን የጉማይ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ2019 E.C የበጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ፣ የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ሞተር ሳይከሎች፣ የመኪና ጥገና እና መለዋወጫዎችን፤ ፈርኒቸሮች ፣ ለመስተንግዶ የሚዉል ምግብ፣ ለጭነት የሚያገለግሉ መኪኖች፣ የሞተር እና የመኪና ጎማ፣ የደንብ ልብስ፣ የግንባታ መሳሪያ፤ ለዉሃ ግንባታ የሚያገለግ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2019
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን የጉማይ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ2019 E.C የበጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ፣ የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ሞተር ሳይከሎች፣ የመኪና ጥገና እና መለዋወጫዎችን፤ ፈርኒቸሮች ፣ ለመስተንግዶ የሚዉል ምግብ፣ ለጭነት የሚያገለግሉ መኪኖች፣ የሞተር እና የመኪና ጎማ፣ የደንብ ልብስ፣ የግንባታ መሳሪያ፤ ለዉሃ ግንባታ የሚያገለግሉ እቃዎች፤ አሸዋ እንዲሁም የጽዳት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በተዘረዘረዉ መስፈርት መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው መሰፈርቶች፡-
1. የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፣
2. በዘርፉ የ2019 ዓ,ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው
4. የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
5. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው
6. ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ በባንክበተረጋገጠ(CPO) ማስያዝ የሚቻል
7. የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 500/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዝብ/ጽ/ቤት መግዛት የሚችል፤
8. ተወዳዳሪዎች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ ማስገባት የሚችል፤
9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒዉን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻዉን እና የድርጅቱን ስም እና ማህተም በማድረግ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያ አንደኛው (21) ቀን 6:00 ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
10. ጨረታዉ በተባለበት ቀን እና ሰዓት ገብቶ ካለቀ በኋላ በእለቱ 6:30 (ስድስት ሰዓት ተኩል) ታሽጎ ተጫራቾችወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ8:00 (ስምንት ሰዓት)በጉማይ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል።
11. አሸናፊ ተጫራቾች ከጽህፈት ቤቱ ጋር ዉል መፈራረም የሚችሉ እና የውል ማስከበሪያ /ዋስትና/ያሸነፈበትን ዋጋ 10% በቼከ ማስያዝ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸዉ።
12. እዚህ ማስታወቂያ ላይ ያልተጠቀሱ መስፈርቶችን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ፡፡ ማሳሰቢያ፡-ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መነቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25917110586/0917016806 ደዉሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጅማ ዞን የጉማይ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
