የኦሮሚያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችንና የተለያዩ መጠን ያላቸውን ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የሽያጭ ጨረታ
ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 03/2017
የኦሮሚያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
- የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችንና
- የተለያዩ መጠን ያላቸውን ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም ድረስ፤
- ኮርፖሬሽኑ አድራሻ ቃሊቲ የመካኒኮችን የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ፊት ለፊት (CCRDA) አጠገብ 3ኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00/ ሦት መቶ/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 – 11፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ንብረቶች ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ባሉበት ቦታ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ኮርፖሬሽኑ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 20% (ሀያ ከመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 251 11439 1057 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኦሮሚያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
