የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት የጥገና መንገዶች እና የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ገልባጭ መኪና እስከነ ሎደሩ ኪራይ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-ደመባ 008/8016
መስሪያቤታችን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት የጥገና መንገዶች እና የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ገልባጭ መኪና እስከነ ሎደሩ ኪራይ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፤ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፤ የመንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መካፈል /መሳተፍ/ የሚያስችል ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል ፕሮፖዛሉንና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በአንድ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ “ኦርጅናል” እና “ኮፒ “ በማለት እና የጨረታ ማስከበርያውንም በተለያየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- ተጫራቾች ለየፕሮጀክቱ ብር 50,000.00 ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበርያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመርያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመርያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
አድራሻ፡- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ወደ ወልቂጤ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ላይ የድሮው የወልቂጤ ከተማ ስፖርተኞች ማደርያ ግቢ ውስጥ እንገኛለን፡፡
ስልክ ቁጥር ፡- +251-113-65-99-32 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን
