Tender Detail

Tender Details

  • Company የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል
  • Address ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0473310841
  • Website
  • Deadline17 Nov 2024, 5:30 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Building Construction

የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኘው አዲስ የዶሮ ቤት ግንባታ የዶሮ ቤት ጥገና እና የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኘው አዲስ የዶሮ ቤት ግንባታ የዶሮ ቤት ጥገና እና የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ነጋዴዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. የኮንስትራክሽን ንግድ ፍቃድ ያለው BC/GC-ደረጃ 5 /አምስት/፡፡
  2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደስ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የምዝገባ የምሰክር ወረቀት ያላቸው እና ካሁን ቀደም በተመሳሳይ ሥራ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማሰረጃ ፎቶ ኮፒ እና ኦሪጅናል ይዞ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የተሟላ ቴከኒካልና ፋይናንሽያል ሠነድ ለየብቻ 1 ኦሪጂናል፣ 2 ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ብር 300,000 /ሦስት መቶ ሺህ ብር /CPO/ የተያያዘበት የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሠነድ በደቡብ ምዕራብ በቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል /ቤት በኩል የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር /በመክፈል ከቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል መግዛት ይችላሉ።
  7. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 31ኛው ቀን 1130 ሰዓት ላይ ታሽጎ 32ኛው ቀን 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
  10. የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
  11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ማንኛውም ኦረጅናል መረጃ ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል፡፡
  12. የጨረታው አሸናፊ 7 ቀናት ውስጥ ውል ገብቶ ሥራውን መጀመር ይኖርበታል፡፡
  13. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር- 0910409901/0934449883 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል

Save Tender