Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethio Life and General Insurance S.C (ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ, ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል በሚወስደው መንገድ ቶሊፕ ሆቴል ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት, Phone: 0114702077
  • Websitehttps://eliginsurance.com/
  • Deadline01 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Vehicle

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ ኢ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ቀላልና ከባድ እንዲሁም ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::


የጨረታ  ማስታወቂያ

ኢትዮ  ላይፍ  ኤንድ  ጀነራል  ኢንሹራንስ  አ.

Ethio Life and General Insurance S.C

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ .. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ቀላልና ከባድ እንዲሁም ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

  1. ተሽከርካሪዎቹን ለመግዛት በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ከቸራሊያ ዝቅ ብሎ በሸዋ ዳቦ 350 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ተሽከርካሪዎች ማቆያ (Recovery Site) ከጥቅምት11 ቀን 2017 . እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2017 . ባሉት የሥራ ቀናት በመምጣት ማየት ይቻላል
  2. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ከጥቅምት 11 ቀን 2017 . እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2017 . ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከቀኑ 11 00 ሰዓት ድረስ ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል በሚወስደው መንገድ ቶሊፕ ሆቴል ፊት ለፊት 4 ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና /ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይቻላል::
  3. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ማዘዣ ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  4. የጨረታው አሸናፊዎች የተሽከርካሪውን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የጨረታ ውጤት በተገለፀ 10 ቀናት ውስጥ ከፍለው 10 ቀናት ውስጥ ንብረቱን ከግቢው ማንሳት ይኖርባቸዋል::
  5. የጨረታ ዋጋ ተንተርሶ ሌላ ዋጋ መስጠት አይቻልም:: የጨረታ ዋጋ አባዝቶ ማቅረብ አይቻልም::
  6. ተሽከርካሪው በጨረታ እስከተሸጠበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር ጨረታውን አሸንፈው የሚገዙ አይጠየቁበትም:: ተሽከርካሪው ከተሸጠ በኋላ የሚፈለግ ግብር ታክስና እንዲሁም ተሸከርካሪው ላይ የሚፈለግ የቦሎ ክፍያና ተያያዥ ቢኖር የገዥው ኃላፊነት ይሆናል::
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልፅ ሁኔታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ነገር ግን ባላቀረቡት ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል::
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ተሽከርካሪውን በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ::
  9. ተጫራቾች ስለተሽከርካሪዎቹ መንገድ ትራንስፖርት በሰጠው ውሳኔና በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል::
  10. ጨረታው ቅዳሜ ጥቅምት 23 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት በኩባንያው ዋና /ቤት ይከፈታል:: ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

       ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549650/0911157195/ 0911153169 ደውለው መረጃ ማግኘት  ይችላሉ::

 

 

Save Tender