ቡራዮ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለኮሪደር ልማት አገልግሎት እና ሴክተር መስሪያ ቤት የሚውሉ ገልባጭ መኪናዎች፣ ደብል ገቢና ፒካፕ መኪና፣ የሕዝብ አውቶቡስ መኪና፤ ቦቴ መኪና (ሻወርትራክ)፤ ባለ ጎማ እስካቫተር፣ ሎደር፣ ቼን እስካቫተር፣ የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ኮሚፓክቴር (Compacter) እና መታወቂያ ለመሥራት የሚያገለግሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት እና ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2017
የቡራዮ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለኮሪደር ልማት አገልግሎት እና ሴክተር መስሪያ ቤት የሚውሉ ገልባጭ መኪናዎች፣ ደብል ገቢና ፒካፕ መኪና፣ የሕዝብ አውቶቡስ መኪና፤ ቦቴ መኪና (ሻወርትራክ)፤ ባለ ጎማ እስካቫተር፣ ሎደር፣ ቼን እስካቫተር፣ የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ኮሚፓክቴር (Compacter) እና መታወቂያ ለመሥራት የሚያገለግሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት እና ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው ላይ መወዳደር ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያለው እንዲሁም በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቡራዩ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በቴሌብር ሒሳብ ቁጥር በተከፈተው 518232 የማይመለስ 2000 (ሁለት ሺህ ብር) ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ የቡራዩ ከፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በማስቆረጥ የቡራዩ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰአት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 በባንክ በተመሰከረለት CPO (ሲፒኦ) እና ትክክለኛ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ አብራችሁ እንድታቀርቡና በቡራዩ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፣ እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት።
- ለማሸነሪ ኪራይ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ነዳጅን፣ ቅባት ጥገናውን እና ሌሎች ተዛማች ወጪዎችን በተጫራቹ ድርጅት (አከራይ) የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ተጫራቶች ጨረታዉን ካሸነፉ በኋላ ማሸነሪዎችን በራሳችሁ ወጪ መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ (ሥራ የሚሠራበት ቦታ) ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለመኪናዎች ኪራይ ለደረቅ መኪናዎች ከከተማው አስተዳደር ወረዳዎች እስከ አሉበት ድረስ ያለውን ርቀት በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ የሚያቀርቡት ማሽነሪ ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ወይም ሕጋዊ የኪራይ ውል አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን 11:30 ሰዓት የሥራ ቀናት ድረስ ሰነዱ የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጨረታው በዚህ ዕለት 4፡ 30 የሚከፈት ይሆናል።
- ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች ለኪራይ የሚያቀርቡት ማሽነሪ አዲስ ሞዴል ከ2016 እና 2017 ወደዚህ መሆን አለበት።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-2604836/ 011-2604879
የቡራዮ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
