ኮፐራዚኔ ኢንተርሽናል (COOPI) ኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በላይ ያገለገሉ 3 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ ከሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በተመለከተው የጨረታ መመሪያ መሠረት መሳተፍ ይችላል፡፡
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 025/2024
ኮፐራዚኔ ኢንተርሽናል (COOPI) ኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በላይ ያገለገሉ 3 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ ከሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በተመለከተው የጨረታ መመሪያ መሠረት መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ በነፃ በመውሰድ መገናኛ አካባቢ ከሚገኘው ቢሮአችን መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ተሸከርካሪዎቹ በሚገኙበት መገናኛ አካባቢ ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 088 ኮፐራዚኔ ኢንተርሽናሌ (COOPI) ኢትዮጵያ ግቢ ውስጥ በመገኘት በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ተሽከርካሪ ዋጋ በጨረታው ሰነድ ሰንጠረዥ ውስጥ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ ጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ኮፐራዚኔ ኢንተርሽናል (COOPI) ኢትዮጵያ ቢሮ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት አንድ ተሽከርካሪ 20 በመቶ /20%/ በኮፐራዚኔ ኢንተርሽናል (Coopl) ኢትዮጵያ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በኮፐራዚኔ ኢንተርሽናል (COOPI) ኢትዮጵያ ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በግልጽ ማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ከተገለጸበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን ክፍያ በመክፈል ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በዚሁ መሠረት የማይፈጽም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱም ይሰረዛል።
- በዚህ ጨረታ አሸናፊ የሚሆኑት ተጫራቾች የባለቤትነት ስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን በመፈጸም ተሽከርካሪውን ይረከባሉ፡፡
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ /ቦንድ/ የጨረታው አሸናፊዎች የሚፈለግባቸውን ክፍያ እንዳጠናቀቁ የሚመለስላቸው ሲሆን በጨረታው አሸናፊ ለሆነ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ከቀሪው ክፍያ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ስለሽያጩ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነድ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- መገናኛ ከቦሌ ክ/ከ ህንፃ ጀርባ ማማስ ኪችን አጠገብ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 088
ስልክ : 0965257371
ኮፐራዚኔ ኢንተርሽናል (COOPI) ኢትዮጵያ
