Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidaama Broadcasting Corporation (የሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን)
  • Address ሀዋሳ ወንዶ ንግድ ኩባንያ ህንጻ ጀርባ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916037261
  • Website
  • Deadline03 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Cargo Vehicle

ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑ ለሥራ የሚፈልጋቸውን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ሞተር ሳይክሎች እና የተለያዩ ዓይነት የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 2017 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑ ለሥራ የሚፈልጋቸውን

        ሎት1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

        ሎት2. ሞተር ሳይክሎች እና

        ሎት3. የተለያዩ ዓይነት የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በዚህ ጨረታ መወዳደር የሚችሉ ፡-

  1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
  3. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው ድርጅቶች ሀዋሳ ሲዳማ ቡና ሕንጻ 3 ፎቅ ላይ በሚገኘው ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመምጣት የተዘጋጀውን ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ብር 200 እየከፈላችሁ እንድትመዘገቡና ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ እንድታቀርቡና የጨረታውን የመወዳደሪያ ዋጋ ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ በሥራ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ቴክኒካል ኦርጅናልና አንዲ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 03 በሚገኘው ጨረታ ሳጥን እንድታስገቡና ጨረታውም 16ኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት የጨረታ ሣጥን ታሽጎ 830 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ሲሆን በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916037261 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን።

 

ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

Save Tender