በዲላ ከተማ አስተዳደር የት/ጽ/ቤት በዲላ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት 4 የመማሪያ ክፍሎች በ2017 በጀት ዓመት በካፒታል በጀት ለማስገንባት ደረጃ BC-5 እና GC-6 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ኮንትራክተሮች በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የቀረበውን መሥፈርት የሚያሟሉ ህንጻ ተቋራጮች መወዳደር ይችላሉ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር Dilla/CW/001/2024/2025
በዲላ ከተማ አስተዳደር የት/ጽ/ቤት በዲላ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት 4 የመማሪያ ክፍሎች በ2017 በጀት ዓመት በካፒታል በጀት ለማስገንባት ደረጃ BC-5 እና GC-6 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ኮንትራክተሮች በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የቀረበውን መሥፈርት የሚያሟሉ ህንጻ ተቋራጮች መወዳደር ይችላሉ።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የንግድ ምዝገባ ም/ወረቀት ያላቸው እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
- የአቅራቢነት ምዝገባ ም/ወረቀት ያላቸው የዘመኑ ግብር ዕዳ ነጻ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግንባታ የምስክር ወረቀት ከክልል ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ማቅረብ የሚችሉ እና ሌሎች ለደረጃው የብቃት ማረጋገጫ እና የሚያስፈልጉ ማስረጃዎችን የጨረታ ሠነዱን ሞልተው ሲያቀርቡ ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ
- ለግንባታ የሚያስፈልገውን የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች ሙሉ በሙሉ ራሱን ችሎ መስራት የሚችል
- ተጫራቾች ለግንባታ የማይመለስ ብር 500 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት ጨረታው እስከሚከፈትበት ዕለት ድረስ በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- የሚሰራውን የግንባታ ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ 70,000 /ሰባ ሺህ ብር/ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ዘግይቶ የመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ኦርጅናል 1 ቴክኒካል 2 ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ፋይናንሻል 1 ኦርጅናል እና 2 ፋይናንሻል ኮፒ እያንዳንዱ ለየብቻ በማሸግ በመጨረሻ ሁሉንም በአንድ እናት በኤንቨሎፕ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ አድራሻቸውን በመሙላት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 የሥራ ቀናት ቆይቶ በ22ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት
