ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለስራ አገልግሎት የሚውል ገልባጭ መኪና (Dump Truck) አቅራቢ ድርጅቶችን በድጋሚ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ ሀገር አቀፍ ግልፅ
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2017
ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለስራ አገልግሎት የሚውል ገልባጭ መኪና (Dump Truck) አቅራቢ ድርጅቶችን በድጋሚ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች ፡-
- በዘርፉ አቅራቢነት የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፤
- ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- በጨረታ ለመሣተፍ ከገቢዎችና ከጉምሩከ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
* የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜና ቦታ ፡-
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሂሳብ ቁጥር 1000604259658 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ሲዳማ ብ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ውስጥ ከሲኮስኮ ቢሮ ቁጥር 513 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላሉ፣
* ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ ፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ ከ8፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡
- በማግስቱ በ12ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል ::
* የጨረታ ዋስትና ፡-
- ማንኛውም ተጫራች 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከስድስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ዋስትና ከኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
* የጨረታ ሠነድ አስተሻሸግ ሁኔታ :-
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ፣ የልዩ እሴት ታከስ ተመዝጋቢነትና የታከስ ከፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተደገፈ CPO/ ብቻ ወይም ከስድስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ከኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ በሰም ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡ ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ቴክኒካል ዶከመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ይህንን አስተሻሸግ ዘዴ ያልተጠቀመ ተጫራች ከጨረታው ይሠረዛል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916071539 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን
