Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Administration Public Recreational Areas Corporation (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115572949
  • Websitehttps://aacaprac.gov.et/?lang=ahm
  • Deadline11 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Building Construction

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን ሎት 1፡- የእንጦጦ ፓርክ ውስጥ የአጥርና የጥበቃ ቤት ግንባታ፤ ሎት 2፡- የእንጦጦ ፓርክ የመንገድ ዳር መብራት ጥገናና አቅርቦት ስራ፤ እና ሎት 3፡- የግንባታ እቃዎች ግዥ፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር 29/2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን፤

ሎት 1- የእንጦጦ ፓርክ ውስጥ የአጥርና የጥበቃ ቤት ግንባታ፤

ሎት 2- የእንጦጦ ፓርክ የመንገድ ዳር መብራት ጥገናና አቅርቦት ስራ፤

ሎት 3- የግንባታ እቃዎች ግዥ፤

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል።

  1. ተጫራቶች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ (clearance) ማቅረብ አለባቸው፤
  2. ተጫራቾች ለየእያንዳዳቸው ሎቶች ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንከ ጋራንቲ በህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ጊቢ ውስጥ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋት 230 እስከ 1130 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻ እና ቴክኒካል ዶክመንት ለብቻ በማሸግ እና ሁለቱንም ለየብቻ ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ በአራት ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 400 ሰዓት ድረስ ለዚህ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 430 ሰዓት ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ጊቢ በግዥና ንብረት ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0115572917 / 0115572949 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የአዲስ  አበባ  ከተማ  አስተዳደር  የህዝብ  መዝናኛ  ቦታዎች  አስተዳደር  ኮርፖሬሽን

Save Tender