የኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በቦታው ላይ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች
የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 006/2017
የኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በቦታው ላይ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ
- ደብረዘይት መንገድ ሳሪስ ከሚገኘው የድርጅቱ ሽያጭ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 - 6፡00 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡00 ሰዓት ብቻ ነው::
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎቹን ሁኔታ እስከ ጨረታው መዝጊያ ጊዜ በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00-10፡30 ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ግቢ ውስጥ በአካል ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 18 ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያቀረቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ ተካቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 18 ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ:‐
በስልክ ቁጥር 0911 86-27-92 በመደወል መረዳት ይቻላል፡፡
ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር
