Tender Detail

Tender Details

  • Company የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቱሉ ኤጀርሳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከጋርመንት ወደ አትክልት ተራ አለፍ ብሎ ከአትክልት ተራ ወደ አባ ገዳ መንገድ ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline29 Dec 2024, 5:30 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቱሉ ኤጀርሳ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው  ያ  ቁጥር  002-2017 ዓ.ም

 

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቱሉ ኤጀርሳ አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት 2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም  መሠረት -

ሎት 1 የደንብ ልብስ ——— የሲፒኦ መጠን 10,000.00

ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች ——— የሲፒኦ መጠን 5,000

ሎት 3 የጽዳት እቃ ——— የሲፒኦ መጠን 10,000.00

ሎት 4 የመኪና ጎማና ጌጣጌጦች ———— የሲፒኦ መጠን 5,000

ሎት 5 ሞንታርቦ ዲኮሬሽን ኪራይ ———— የሲፒኦ መጠን 3,000.00

ሎት 6 የህዝብና የጭነት ትራንስፖርት ————

ሎት 7 የቢሮ እቃዎች ጥገና ————

ሎት 8 ቋሚ እቃ ————

ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት - በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች አቅራቢዎች

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  2. የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ በእያንዳንዱ ሎት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት 7 በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፋይናስ /ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ (ኤንቨሎፕ) ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በፋይናንስ /ቤት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን 1130 ታሽጎ 11ኛው ቀን ከረፋዱ 430 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የመፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸውና ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች እንዲሁም ለቋሚ እቃዎች /ቤቱ ባዘጋጀው የፍላጎት መግለጫ መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. አቅራቢዎች ለተወዳደሩበት እቃዎች ውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. አምራች የሆናችሁ አቅራቢዎች ካደራጃችሁ አካል /ተቋም/ በሚመለከተው አካል የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ እና አምራች ስለመሆናችሁ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት ትችላላችሁ።
  11. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል
  12. የዘገየ ተጫራችና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. አድራሻ - ///ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ /ቤት ከጋርመንት ወደ አትክልት ተራ አለፍ ብሎ ከአትክልት ተራ ወደ አባ ገዳ መንገድ ገባ ብሎ፡፡

 

በንፋስ  ስልክ  ላፍቶ  ክፍለ  ከተማ  የወረዳ  14  ሉ  ኤጀርሳ  ፋይናንስ  /ቤት

 

Save Tender