በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና የመኪና ጎማ ከነከመናዳሪው፣ የእንሰሳት መድሃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች መግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት፡-
ሎት 1፡- የጽህፈት መሳሪያ
ሎት 2፡- የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና የመኪና ጎማ ከነከመናዳሪው
ሎት 3- የእንሰሳት መድሃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማሳተፍና
በማወዳደር ዝቅተኛ ዋጋ ከሰጠው ድርጅት አሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በመፈፀም መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ፣ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ። ማስረጃቸውን ማቅረብ የሚችሉ።
1. የዘመኑን የታደሰና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መሞላት የሚገባውን መረጃ ሁሉ በትክክል በመሙላት እና በመፈረም አንድ ኦርጅናል ፖስታ የራሳቸውን ፊርማና አድራሻ ተፅፎበት ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻው በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር ብቻ) ቢሮ ቁጥር 20 በመግዛት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም።
4. ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም፤ሁሉም እቃዎች መሞላት አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በቁርጥ ለጽህፈት መሳሪያ 35000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር) የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና የመኪና ጎማ ከነከመናዳሪው 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር) እና ለእንሰሳት መድሃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች 30000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማሲያዝ አለባቸው።
6. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትይሆናል
7. በሎት 3 ላይ የተጠቀሰው የእንስሳት መድሀኒት እና መገልገያ መሳሪያዎች ግዥን በተመለከተ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ጅምላ አከፋፋዮች ብቻ በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ይሆናል።
8. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ 10% የውል ማስከበሪያ በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ማስያዝ እና ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል።
9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-637-50-23 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ደ/ብርሃን
