የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በሎት ከፋፍሎ ግዢ ለመፈጸም የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጭ ተወዳዳሪዎችን ብቻ ለጨረታ ይጋብዛል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 05/2017
የግዥው አይነት
ሎት 1 ባለ 4 ኮከብ ሆቴል አገልግሎት ግዥ
ሎት 2 የዲጂ አገልግሎት ግዥ
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያለውና የ 2016 የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ ያላቸው::
- ለእቃ አቅራቢነት ስለመመዝገባቸው እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) ወይም በባንከ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ስም CPO (ጋራንት ቢድ ቦንድ) በማሰራት ማስያዝ የሚችሉ።
- የጨረታ ማስከበርያ ዋስትናው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከመጨረሻው ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ ይቆያል::
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የሚይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ቢሮው በሰጣችሁ ፎርማት ላይ በመሙላት እና የድርጅታችሁ ማህተም ፤ ፊርማና ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ፡-
- ፋይናንሽያል አንድ ኦርጅናል እና ፋይናንሽያስ አንድ ኮፒ
- ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ቴክኒካል አንድ ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በተለያዩ ፖስታዎች ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ለሎት 2 ቢሮው በሚያቀርበው ዝርዝር (ናሙና) መሰረት ማቅረብ የሚችል
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡30 – 11፡00 ሰዓት ድረስ የግዥ ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 803 በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸኋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ማለትም የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት (ማቅረብ) አይቻልም።
- ቢሮው ብዛቱን በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት መቀነስና መጨመር የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0118126179/0111703024/ በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ውቤ በረሃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ
