የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለጎንደር ከተማ አስ/ጤና መምሪያ በማራኪ ክ/ከተማ የአየር ጤና ቀበሌ የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል የህንጻ ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለጎንደር ከተማ አስ/ጤና መምሪያ በማራኪ ክ/ከተማ የአየር ጤና ቀበሌ የጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል የህንጻ ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡
ማቅረብ የምትችሉት መረጃዎችም፤
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፤
- የህንጻ ግንባታውን ለማሰራት ለጠቅላላ ስራ ተቋራጪ ደረጃ 7 እና ከዘያ በላይ ለህንጻ ስራ ተቋራጪ ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ መሆን አለባቸው፤
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የሚገነባውን የግንባታ የስራ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጎን/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጎን/ከ/አስ/ግዥና/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን፣ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው::
- ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች ቁጥር ቢያንስ 3 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት /አርቲሜቲክ ቼክ/ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5% ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል፤ እንዲሁም ከ3 በታች ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት /አርቲሜቲክ ቼክ/ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 1% ድረስ ብቻ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት በጎንደር ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጥሪያችንን አክብረው ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት ይከፈታል፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለው ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ማቅረብ የሚችል ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ መ/ቤታችን የማይቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 03 06 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአብክመ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን
