በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለቡልጋ ከተማ አስተዳደር የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የውሃ ታንከር ግንባታ ለማሠራት የሚፈልግ በመሆኑ በዘርፉ የተሠማሩና በደረጃ 5 /አምስት እና በላይ የሆኑ ህጋዊ ተቋራጭ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡-04/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለቡልጋ ከተማ አስተዳደር የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የውሃ ታንከር ግንባታ ለማሠራት የሚፈልግ በመሆኑ በዘርፉ የተሠማሩና በደረጃ 5 /አምስት እና በላይ የሆኑ ህጋዊ ተቋራጭ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች መሥሪያ ቤቱ ባወጣው የውሃ ታንከር ግንባታ የፍላጎት ዝርዝር መግለጫ /ቢል ኦፍ ኳንቲቲ/ መሠረት የመጫረቻ ሰነዳቸው ቴክኒካልና ፋይናንሺያል በሚል ተለይቶ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማቅረብ በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች፡-
- በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ስለሚሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሠማሩ ሆነው በደረጃ 2 እና በላይ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 12 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ 22ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሠዓት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ሥም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለ60 ቀናትና እንዲሁም ለተጨማሪ 20 ቀናት ጸንቶ መቆያ ተጨምሮ በድምሩ ለ80 ቀናት ሆኖ መሰራት አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በጥንቃቄ የቴክኒካልና የፋይናንሽያል በሚል ለየብቻው አንድ ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማሰታወቂያው ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ22ኛው ቀን በ4፡01 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የመሰብሳቢያ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በሌላኛው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይችሉም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011-6-81-32-41/ 011-6-81-63 96 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ
