Tender Detail

Tender Details


የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የግንባታ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡


ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የግንባታ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

1፡- በዞብል ከ/ከተማ የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ ስራ ለማሰራት ከደረጃ 8 በላይ የሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የከተማ አስተዳደሩ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሞሉ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን

1.     በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው /ያላት/

2.    የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN /ያለው/ያላት

3.    ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

4.    ተጫራቾች በጨረታ ሲያስገቡ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው

5.    የሚሰሩ ስራዎች ዓይነትና እስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ

6.    ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺ/ ሲሆን በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.አ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

7.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 21 ማግኘት ይችላሉ

8.    ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጎ/ከ/አስ/ከ/መ/ል/መምሪያ ግዥናፋ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 23 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ

9.  ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ24/12/2018 ዓ.ም እስከ 9/1/2019 ዓ/ም ድረስ ሲሆን መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ4፡00 ስዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡

10.  የጨረታውን ሰነድ ሲሞሉ የሥራው ዝርዝር ዋጋ ሙሉ በሙሉ መሞላት አለበት ለርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ደግሞ ውድቅ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈስገዎት ገ/ከ/ስስ/ከ/ስ/ኮ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 06 በስካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0918712038 ደውስው ማረጋገጥ ይችሳሱ::

 

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Gondar City Administration seeks bids for construction of low-income housing in Zobel sub-city. Bidders must hold a valid trade license, TIN, and VAT registration. Work details are in the tender document.
Save Tender