የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በ2017 በጀት ዓመት የሚገለገልባቸውን ዕቃዎችን እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በ2017 በጀት ዓመት የሚገለገልባቸውን ዕቃዎችን እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ፡-
ሎት 1. የቀረፃ መድረክ ግንባታ የሚሆን ኢቨንት ኦርጋናይዘር አገልግሎት
ሎት 2. ዲጂታል መታወቂያና ባጅ ማተሚያ ማሽን ግዥ በድጋሚ የወጣ
በጨረታ ቁጥር አ.ሚ.ኔ.ብ.ግ.ጨ.007/2017 በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የገቢዎች ክሊራንስ ያላቸው::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና በግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና ፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለእያንዳንዱ ለሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 ለሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት 1 እና ለሎት 2 ጨረታዎች 10 በሥራ ቀናት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቢሮ ቁጥር 28 የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የ በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርከ ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም። የመክፈቻው ዕለት በዓል/ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን /ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ፣ ፋይናንሻ ኦሪጂናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- በጨረታው ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡-
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ህንፃ ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0111116382 መደወል ይችላሉ፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
