የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውል በሎት አንድ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች በሎት ሁለት ቋሚ ዕቃዎች/ኤሌክትሮኒክስ ማለትም ላፕቶፕ እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች/፣ በሎት ሦስት አላቂ የጽዳት ዕቃዎች እና በሎት አራት የደንብ ልብስ ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 04/2017
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውል በሎት አንድ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች በሎት ሁለት ቋሚ ዕቃዎች/ኤሌክትሮኒክስ ማለትም ላፕቶፕ እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች/፣ በሎት ሦስት አላቂ የጽዳት ዕቃዎች እና በሎት አራት የደንብ ልብስ ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ ከሃምሳ ሺህ ብር በላይ ላላቸው ግዢዎች የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግስት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ከባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት የቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለሰላሳ /30/ ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ነው፡፡
- አቅራቢዎች ጨረታውን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሎት አንድ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ፣ ለሎት ሁለት ብር 15,000.00/ አስራ አምስት ሺህ ብር ፣ ለሎት ሦስት ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ እና ለሎት አራት ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በባንከ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው መሠረት አቅራቢው በፈለገው በአንዱ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ዋስትና መልከ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
በደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን የግብዓት አቅርቦት ባለሥልጣን አስ/ደ/ሥራ ሂደት የፖስታ ሳጥን ቁጥር
404 ስልክ ቁጥር :- 046-13-15-012/0916866262/0923690085
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
