በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በጭሮ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የጭሮ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በጭሮ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ
አላቂ እና ቋሚ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
ኤሌክትሮኒክሶች፣
የጽዳት እቃዎች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች ላፕቶፖች፣
ለትምህርት መርጂ አገልግሎት የሚውሉ ጠመኔዎች እና ሌሎችንም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የታደሰና የዘመኑን/ 2018 ዓ/ምን/ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000/ ሃያ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼከ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ በተረጋገጠ ቼክ አቅራቢዎችም ከላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን 20,000/ ሃያ ሺህ /ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ (CPO) የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ ከVAT ጋራ በመጥቀስ በታሸገ ኢንቨሎፕ ውስጥ አድርገው እስከ መስከረም 07/01/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በቢሮ ቁጥር 3 ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚያኑ አለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ መስከረም 07/01/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከዚህ በላይ በተገለጸው ጽ/ቤት አድራሻ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት በአካል በመቅረብ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ መግዛት ይችላሉ።
6. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ጭሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊው ድርጅት እቃዎቹን በተጠየቀው ብዛትና ጥራት የማቅረብ ግዴታ አለበት።
7. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል።
9. ለሽያጭ የቀረበው እቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ድርጅቱ በራሱ ወጪ እቃውን የመለወጥ ወይም ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት።
10. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
11. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው መሆን አለባቸው።
12. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ ባሸነፉበት የእቃ ዓይነት ሙሉ በሙሉ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
13. መስሪያ ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ ሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም።
14. ተጫራቾች ያሸነፉበትን 10% የውል ማስከበሪያ (Performance Band) ማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።
15. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር (suppliers List) መመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
16. ተጫራቾች በኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዢ ድህረ ገጽ (Electronics Government Procurement) EGP ላይ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አድራሻችን ምዕ/ሐ/ዞን/ ጭሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 0911950343/0255511314
የጭሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
