Tender Detail

Tender Details


የአርባምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚሰጡ ከታች በምድባቸው በዝርዝር የተገለጹትን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።


የጨረታ ማስታወቂያ

የአርባምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚሰጡ ከታች በምድባቸው በዝርዝር የተገለጹትን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ። በዚህም መሰረት

  1. 1ኛ ሎት ምድብ አንድ (ለሠራተኛ የልብስ ሳሙና 250ግ (የገላ ሳሙና 250ግ እና ሶፍት እንዲሁም
  2. 2ኛ ሎት ምድብ ሁለት ለቢሮ የሚሆን Electronic ዴስክቶፕ ኮምፕዩተር ፕሪንተርና ላፕቶፕ ኮምፕዩተር ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው
  3. ከላይ በተጠቀሰው ዕቃ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ እንዲሁም በዘርፉ በቀጥታ ተሳታፊ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ
  4. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒሰቴር የዕቃ አቅራቢ ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ መኖሩን የሚገልጽ ማስረጃ
  5. በሚወዳደሩት የዕቃ ዓይነቶች ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ዓይነት ለውድድር ሲመጡ በየአይነታቸው አንዳንድ ሳምፕል ማቅረብ የሚችል እንዲሁም ተወዳድሮ ሲያሸንፍ ያሸነፋቸውን ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ድርጅቱ እስቶር ድረስ በማቅረብ የጫኝና አውራጅ ችሎ ማስረከብ የሚችል፡፡
  6. ከላይ በሎት አንድ ምድብ አንድ እና በሎት ሁለት /ምድብ ሁለት በሚወዳደሩት የዕቃ ዓይነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች ብር 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ዶክመንት ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ከፍሎ ከድርጅቱ በመውሰድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል ለብቻ ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ ለብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል ለብቻ ፋይናንሻል ዶክመንት ኮፒ ለብቻ አሽጎ ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአርባምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግቢ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች /ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል ፡፡ ሆኖም የጨረታ መዝጊያና መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡ በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም ።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡ ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 0468810369/0468812049 መደወል ይቻላል ፡፡

የአርባምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Arba Minch City Water and Sewerage Service seeks bids for two lots: Lot 1 (soap for staff) and Lot 2 (desktop computers, printers, laptops). Bidders need a valid trade license, tax compliance, VAT registration, and supplier registration certificate.
Save Tender