ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ብዛት 23 ሞተርሳይክሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
MIDROC INVESTMENT GROUP
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር HP/OT/01/2017
- ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ብዛት 23 ሞተርሳይክሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
መካኒሳ አቦ ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው
ኪዊንስ ሱፐር ማርኬት ሳራ ቅርንጫፍ ጎን
በሚገኘው ህንጻ የሀገር ውስጥ ግዥ ዋና ክፍል
ስልክ ቁጥር 0913851598 ወይም 0911314547
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ፖስታ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ሰ.ፒኦ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዕቃዎቹ ርከከብ የሚፈፀመው አዲስ አበባ በሚገኘው ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር መጋዘን ነው::
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለሰላሳ (30) ቀናት ይሆናል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
