Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው የሚያስፈልጉ አጠቃላይ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ሞተር ሳይክሎች፣ የመኪና እና የሞተር ጎማዎች፣ የህንፃ መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ውሃ ዕቃዎች፣ የመኪና እስፔርፓርቶችና የእንሰሳ መድሀኒቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው የሚያስፈልጉ አጠቃላይ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ሞተር ሳይክሎች፣ የመኪና እና የሞተር ጎማዎች፣ የህንፃ መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ውሃ ዕቃዎች፣ የመኪና እስፔርፓርቶችና የእንሰሳ መድሀኒቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለውና ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችል ፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. በኢጂፒ (e-GP) ፖርታል የተመዘገበና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) ከዚህ በታች በተዘረዘረው ሰንጠረዥ መሰረት በጉመር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ኦሪጅናል ዶክመንት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተ.ቁ የግዢው አይነት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን
1 የጽህፈት መሳሪያ 40,000 /አርባ ሺህ ብር
2 የኤሌክትሮኒከስ 40,000 /አርባ ሺህ ብር
3 የፈርኒቸር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር
4 የአልባሳት 20,000/ ሀያ ሺህ ብር
5 የህ/መሳሪያ 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር
6 የሞተር ሳይከሎች 40,000 /አርባ ሺህ ብር
7 የመኪና ጎማዎች 40,000 /አርባ ሺህ ብር
8 የሞተር ጎማዎች 20,000 /ሀያ ሺህ ብር
9 የፅዳት ዕቃዎች 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር
10 የእንሰሳ መድሀኒቶች 20,000 /ሀያ ሺህ ብር
11 የመኪና እስፔርፓርቶች 15,000/ አስራ አምስት ሺህ ብር
12 ውሃ ዕቃዎች 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር
  1. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን የአየርላይ ቆይታ በኋላ በ22ኛው ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት 8፡30 ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡
  2. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  3. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጉመር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ ብር 300/ሶስት መቶ በመከፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
  4. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ከላይ በተራ ቁጥር 1--6 ላይ የተገለፁት ዶከመንቶች መረጃዎች ዋናው እና ሁለት(2)ኮፒው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ መከፈቻ ቀን ቅዳሜ፣እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይዛዋወራል

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡-0113110082/ 0113110101/0953339353

አረቅጥ

በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Procurement of office supplies, clothing, electronics, furniture, motorcycles, vehicle/motorcycle tires, building equipment, cleaning items, water equipment, vehicle spare parts, and veterinary medicines for Gumer District, Central Ethiopia. Bidders must hold valid business licenses, TIN, VAT registration, and e-GP supplier registration.
Save Tender