በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎዴ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ 24 የወንበር ልክ ያለው 1 (አንድ) መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በጨረታ አወዳድሮ ላልተወሰነ ጊዜ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቲ-01
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎዴ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ 24 የወንበር ልክ ያለው 1 (አንድ) መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በጨረታ አወዳድሮ ላልተወሰነ ጊዜ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን በማሟላት መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣የባለቤትነት ደብተር ሊብሬ ፣ የመድን ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሃገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000496010117 ERA GODE DISTRICT ገቢ በማድረግ በጎዴ መ.ጥ.ዲስትሪክት ግዥ ፣ አቅ.ን.አስ.ቢሮ ቁ.5 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ ጎዴ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ሲሆን የተሸከርካሪው የስሪት ዘመን እ.ኤ.አ. ከ 2002 ጀምሮ መሆን አለበት፡፡የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ክፍት ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን በዲስትሪክቱ ግዥ፣ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠርነ 16ኛ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከብር 10.000 (አስር ሺህ) ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በዚጋዜጣ ቼክ ወይም በገንዘብ ያዥ በተፃፈ ቼክ (CPO) ከሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጎዴ መ.ጥ.ዲስትሪክት ቢሮ ቁጥር 10 በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው:: ከጨረታ መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
በኢትዩጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎዴ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
ግዥ፣ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን
ስ.ቁ. ሞባይል 0777004329 /0939153509
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎዴ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
