Tender Detail

Tender Details

  • Company ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር
  • Address ኢትዯጵያ, Phone: 09-11-24-63-12
  • Website
  • Deadline01 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Construction Works

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ-01 ለሚገኘው ለነባር አጠቃላይ ንግድ ስራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ማጠናቀቅ የሚችሉ እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የጨረታውን ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።


 

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር :- NGTSC/R/001/2017

 

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ-01 ለሚገኘው ለነባር አጠቃላይ ንግድ ስራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ማጠናቀቅ የሚችሉ እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የጨረታውን ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

 

ተ.ቁ

የፕሮጀክት ስም

የሚገኝበት ቦታ

 

የጨረታ ዋስትና ብር መጠን

የተቋራጭ ደረጃ

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

1.

የነባር አጠቃላይ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር B+2+G+4 ህንጻ Renovation (Civil Work)

አዲስ ከተማ /ከተማ ረዳ 01 መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ

350,000

GC-3/BC-2 እና በላይ

90 ቀን

 

  1. 2017 . የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፤ ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን / የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም 2017 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፤ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list) ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::
  2. ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሺያል አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፊርማ፣ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የታሸገውን 3 ፖስታ የቴክኒካል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት (Calendar Days) የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 230 እስከ 1100 ሰዓት ድረስ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ-01 መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በነባር አጠቃላይ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ ላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000184750507 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ የገቢ ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመቁጠሪያ ቀን (Calendar Days) በመቁጠር 16ኛው የስራ ቀን (Working Days) 400 ሰዓት ድረስ  በነባር አጠቃላይ ንግድ ስራ አከሲዮን ማህበር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት 430 ሰዓት ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ማሳስቢያ - የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 16ኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 400 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 430 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡

  1. ተጫራቾች 90+28 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) በባንከ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና / UNCONDITIONAL BANK GUARANTE በነባር አጠቃላይ ንግድ ስራ አከሲዮን ማህበር ስም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::
  2. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጣነ (unbalanced Bid) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
  3. ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Hate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
  4. በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መመሪያን በሚያዘው መሠረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ በጽሑፍ ወደም

በስልክ ቁጥር:- +251-9-45-98-68-45/ +251-9-11-24-63-12 ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 መርካቶ፣ ሸማ ተራ አካባቢ ነባር አጠቃላይ ንግድ

አክሲዮን ማህበር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ፡፡

 

ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር

 

Save Tender