የአ/አበባ ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የስፖርት ትጥቅ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር AAPC NCB 006/2017 ዓ/ም
የአ/አበባ ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የስፖርት ትጥቅ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን ፡-
|
ሎት |
የጨረታ ዓይነት |
የናሙና መለያ |
የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን |
|
|
001 |
የተለያዩ የስፖርት ትጥቅ |
በኮሚሸኑ ፍላጎት መሰረት ናሙና የሚቀርብበት |
50,000 |
00 |
ስለዚህ ፡- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፣
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሰ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት መቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት።
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናሻል/ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ በትክክል መፃፍ እንዲሁም ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ፣ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ. ከቴክኒክ ሰነዶችጋርበአንድላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ወይም በከፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
- በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ያቀረቡአቸው ዕቃዎች ኮሚሽኑ ባወጣው ፍላጎት መግለጫ/specification መሰረት መሆኑን በኮሚሽኑ የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል
- ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ6ኛው ቀን እስከ ጠዋት 4፡30 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በኮሚሽኑ ግዢና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- በጨረታ ሰነዱ ክፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን ከጠዋት 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 5፡00 ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4፡30 ሰዓት ታሽጎ ታሽጎ 5፡00 ሲሆን ይከፈታል።
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም። አሸናፊ ድርጅት ያለፈባቸውን ትጥቀቆች የስራ ትዕዛዝ ከተሰጠበት ቀን አንስቶ በ5 ቀን ውስጥ ማስገባት የሚችል
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥ፡- 011862-58-00(011 111 448) የአ/አበባ ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ
