Tender Detail

Tender Details


በኮ/ቀ/ከ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የስራ ዘመን ከዚህ በታች በሎት የተደራጁ እቃዎችን በጠኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በኮ/ቀ/ከ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የስራ ዘመን ከዚህ በታች በሎት የተደራጁ እቃዎችን በጠኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1-የፅህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 2-የስፖርት እቃዎች
  • ሎት 3. የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 4. የደንብ ልብስ
  • ሎት 5. የላብራቶሪ እቃዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና አጋዥ መፅኀፍቶች
  • ሎት 6. የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 7. የቢሮ መገልገያ ቋሚ እቃዎችና
  • ሎት 8. የተለያዩ ጥገናዎች
  • ሎት 9 የትራንስፖርት ስራዎች
  • ሎት 10. መስተንግዶ

በመሆኑም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የረጲ አጠቃለይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኮ/ቀ/ክ/ ከተማ ወረዳ 02 አለፍ ብሎ ካራቆሬ አካባቢ አጃንባ መውጫ አካባቢ ቢሮ ቁጥር 71 ቀርበው መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡

  1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዝጋቢዎች መሆን አለባቸው፡፡
  4. ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ጊዜው ያላላፈ ከገቢዎች ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የአቅራቢነት ምዝገባ በኦላይን የተመዘገበ መሆን አለበት
  6. የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች ደብዳቤው ባደራጃቸው ኃላፊ የተፈረመ እና አምራች ድርጅት መሆናቹን የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ
    • ሎት 1:- 33,500.00/ሰላሳ ሶስት ሺ አምስት መቶ ብር
    • ሎት 2:- 32,000.00/ሰላሳ ሁለት ሺ
    • ሎት 3፡- 32,000.00/ሰላሳ ሁለት ሺ ብር
    • ሎት 4- 33.500.00/ሰላሳ ሶስት ሺ አምስት መቶ ብር
    • ሎት 5፡- 8,000.00/ስምንት ሺ ብር
    • ሎት 6:- 50,000.00/ሃምሳ ሺ ብር
    • ሎት 7-9700.00/ዘጠኝ ሺ ሰባት መቶ ብር
    • ሎት 8:- 8,000.00/ስምንት ሺ ብር
    • ሎት 9:- 8000.00/ስምንት ሺብር
    • ሎት 10:- 29,000/ሀያ ዘጠኝ ሺ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  11. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  13. ገዢው በአካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  14. ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነድ ውስጥ የተካተተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 10 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ሲፒዮ አሰርተው ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
  15. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል/ተመላሽ አይደረግም/
  16. የእቃ ማስረከቢያ ቦታ ረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ይሆናል፡፡
  17. በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክቁጥር መኖር አለበት፡፡
  18. ት/ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6ወር ድረስ ውሉን ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሚቆጠር10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ከፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በረጲ 2ኛ ደ/ት/ቤት በሂሳብ ከፍል ቢሮ ቁጥር 71 ውስጥ ይከፈታል፡፡
  20. የዕቃ ማጓጓዣብር አሸናፊው ተጫራች ይሸፍናል፡፡
  21. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- በኮ/ቀ/ከ/ከ ወረዳ ከ የረጲ 2ኛ ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ሲሆን ለበለጠ መረጃ 0113488850/0113694156

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for purchasing goods organized into 10 lots: office supplies, sports equipment, cleaning items, clothing, laboratory/teaching materials, office electronics, fixed office furniture, various repairs, transport services, and catering. Bidders must hold valid trade licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier registration. Samples required.
Save Tender