የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ሎት -1 የደንብ ልብስ ፣ ሎት 2 ለጽሕፈት መሳሪያ እና ሎት ፡- 3 የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አስ/ዲ/ግ/ሥ/ቢሮ 002/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ሎት -1 የደንብ ልብስ ፣ ሎት 2 ለጽሕፈት መሳሪያ እና ሎት ፡- 3 የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፤
- ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን አገልግሎት ለመስጠት በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ የያዙና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ መለያ ቁጥር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች አገልግሎቱን ለማቅረብ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ለደንብ ልብስ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ሎት፡-2 ለጽህፈት መሳሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 3 ለመኪና ጌጣጌጥ ዕቃ ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን አሟልቶ ኮፒና ኦርጅናል በማድረግ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 /አስር/ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 11ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11-04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ለእያንዳንዱ ሎት ሳምፕል ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ /ሲፒኦ/ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሑፍ በሰባተኛው ቀን አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም አለበት፡፡ ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ውል ከፈፀሙ በኋላ እቃውን በውሉ መሠረት በሚፈለግበት ቦታ እና ሰዓት የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- 6 ኪሎ አዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ህንጻ ላይ
ስ.ቁጥር ፡- 011 154 1475/011 154 19 12
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ
