የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ሎት፡ 1 ሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት፣ ሎት፡ 2 ፎቶ ኮፒ፣ ላፕቶፕ እና የፕሪንተር ማሽን ጥግና እና ሰርቪስ፣ እና ሎት፡ 3 የኮንስትራከሽን ግንባታ ላቦራቶሪ መመርመሪያ ማሽኖች መለዋወጫ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/አስ/ዲ/ግ/ሥ/ቢሮ 003/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ
ሎት፡ 1 ሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት፣
ሎት፡ 2 ፎቶ ኮፒ፣ ላፕቶፕ እና የፕሪንተር ማሽን ጥግና እና ሰርቪስ፣
ሎት፡ 3 የኮንስትራከሽን ግንባታ ላቦራቶሪ መመርመሪያ ማሽኖች መለዋወጫ እቃዎች
ስለሆነም ፡
- ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን አገልግሎት ለመስጠት በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ የያዙና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ መለያ ቁጥር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች አገልግሎቱን ለማቅረብ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት፡- ሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር፣ ሎት፡- 2 የፎቶ ኮፒ፣ ላፕቶፕ እና የፕሪንተር ማሽን ጥገና እና ሰርቪስ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር፣ ሎት፡-3 የኮንስትራክሽን ግንባታ ላቦራቶሪ መመርመሪያ ማሽኖች መለዋወጫ እቃዎች፣ ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሰራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከኛ ፎቅ በመቅረብ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን አሟልቶ ኮፒና ኦርጅናል በማድረግ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 አስር ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 11ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11-04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው በ11ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ሲፒአ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሑፍ በሰባተኛው ቀን አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም አለበት፡፡ ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ውል ከፈፀሙ በኋላ እቃውን በውሉ መሠረት በሚፈለግበት ቦታ እና ሰዓት የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- 6 ኪሎ አዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ህንጻ ላይ
ስ.ቁጥር፡- 011 154 1475/011 154 19 12
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ
