የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የጉምሩክ ቀረጥ የተከፈለባቸው የተለያዩ ሞዴል ያላቸው 14 /አስራ አራት/ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የጉምሩክ ቀረጥ የተከፈለባቸው የተለያዩ ሞዴል ያላቸው 14 /አስራ አራት/ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ፡-
የተሽከርካሪዎቹን ሁኔታ በድርጅቱ በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታ ሰዓት ድረስ ማየት ይቻላል።
የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ተሽከርካሪዎቹን የሚገዛበትን ዋጋ 10% ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ገቢ ማድረግ ወይም በሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎኘ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
ጨረታው የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111 416 3978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
