የለሚኩራ ከ/ከተማ የወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ ሊያሰራ ላቀደው የማስፋፈያ ግንባታ ስራዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ (G.C6 & ABOVE) ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/መ/ጤ/ጣ/002/2017
የለሚኩራ ከ/ከተማ የወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ ሊያሰራ ላቀደው የማስፋፈያ ግንባታ ስራዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ (G.C6 & ABOVE) ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ለስራው ፍቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ 'የ2017 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ተቋራጮች መሆን ይጠበቅባቸዋል ተጫራቾች ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ወረዳ 08 አሞራው መታሰቢያ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 48 ድረስ በመምጣት ይህ ጋዜጣ ካወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናቾች ውስጥ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተቋራጮች ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናሽያል ሰነድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በሰም የታሸገውን 6 ፖስታ የፋይናሽያል ሰነድ ሶስቱን የፋይናንሽያል ሰነድ ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ እና ቴክኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ የርPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩትን የስራ አይነት ስም በመፃፍ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አሞራው ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 48 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን በ11 (አስራ አንደኛ ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ሰነድ Technical /proposal እና ፋይናንሽያል ስነድ /Financial proposl/ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚሁ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ የቅድመ ብቃት /Technical proposal /በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 8 አሞራው መታሰቢያ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 48 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ውል ያቋረጠ ተወዳድሮ ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስገቢያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURIY) 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፣ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አሞራው መታሰቢያ ጤና ጣቢያ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ ፣ የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ ፣ዋጋ (Rate) ያልተሞላበት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
- ከትንሹ ግምት በታች እና የተጋነነ ዋጋ ያስገባ ተቋራጭ ብሬክዳውን (BREAKDOWN ) ማስገባት እንደሚገደድ እናሳውቃለን፡፡
- የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ አሞራው ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቆ ቢሮ ቁጥር 48 በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 90 ቀን ነው፡፡
ማሳሰቢያ ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
አድራሻ ፡- ከፊጋ መብራት ወደ ሲኤምሲ በሚወስደው መንገድ ላይ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 48 ላይ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የለሚኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ
