በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ከተማ አስተዳደር ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ለባቲ ከ/አስ/ከተ/መሰ/ልማ/ቤ/ኮ/አገ/ ጽ/ቤት ለሚመራው የተለያዩ ግንባታ ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ከተማ አስተዳደር ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ለባቲ ከ/አስ/ከተ/መሰ/ልማ/ቤ/ኮ/አገ/ ጽ/ቤት ለሚመራው የተለያዩ ግንባታ ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል።
- ሳይት 1- የባቲ ከ/አስ/03 ቀበሌ ከአፍዴራ ቦኔ ወንዝ 02 ቀበሌ ትኩየ ወፍጮ አካባቢ፣ ውሀ ልማት እና ጤና ጣቢያ መንገድ እንዲሁም ሌሎች የሚፀዱ ቀበሌ ተፋሰስ እና ካልቨርት ጥገና ግንባታ
- ሳይት 2–የባቲ 02 ቀበሌ G+4 ገበያ ማእከል እስከ 1ኛ ፎቅ ግንባታ
- ሳይት 3 gravel rode maintenance (የጠጠር መንገድ ጥገና ከትኩዮ ወፍጮ እስከ ዐ4 ቀበሌ እና ወረዳ ግብርና) ሳይት 4 ኮብልስቶን ጥገና የባቲ 01 ቀበሌ አካባቢ 02 ጫት ተራ፣ ጅዳ ሰፈር፣ ውሃ ልማት፣ አረፋ ጎራ፣ 03 አጣሪ ገንዳ፣ ጉልት አካባቢ፣ ህዳሴ ማህበር እና ሆስፒታል መንገድ ኮብልስቶን ጥገና፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች የንግድ ፈቃዳቸው በጀርባው የሚገልፅ ካለው ኮፒ አድርገው ያያይዙ
- የግብር መለያ ቁጥር ወይም TIN NO ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ተጫራቾች እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁ. 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ አድርጎ ማቅረብ የሚችል፣
- ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለሳይት 1፣ ሳይት3 እና ሳይት4 ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ ሲሆን ለሳይት 2 -የባቲ 02 ቀበሌ G+4 ለገበያ ማእከሉ እስከ አንደኛ ፎቅ ግንባታ G-6 እና ከዛ በላይ የሆነ ጠቅላላ ግንባታ ስራGC ንግድ ፍቃድ ያለው ወይም ያላት እና በዘርፉ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፣
- የሚሰሩ የግንባታ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለሰ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁ.6 ከዋና ገ/ያዥ ላይ መግዛት ይችላሉ፡፡ የሚወዳደሩበት ሰነድ የያዘው ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩት ቁርጥ ዋጋ ሳይት1 18000 /አስራ ስምንት ሺ ብር/ ሳይት2. 250,000/ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ብር/ ሳይት3. 60,000/ስልሳ ሺ ብር/ ሳይት4 7,500 /ሰባት ሺ አምስት መቶ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ወይም cpo ወይም ቢድ ቦንድ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባቲ ከተማ ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በመሂ1. ገቢ አድርጎ ከዋና ጨረታ ሰነድ ጋር ፖስታ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ አለባቸው፣በእጅ cpO ይዞ መቅረብ አይቻልም።
- ይህ ግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀን ከ 07/06/2017 እስከ 27/06/2017 የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰአት ድረስ ከጽ/ቤቱ ገ/ያዥ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ይህ ግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 22ኛው ቀን ላይ በ 28/06/2017 በ3፡30 ሁሉም ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን ሳይት 1 እና ሳይት 2 ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ሳይት 3 ሳይት 4 ከጠዋቱ 5፡30 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባቲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት ሳይገኙ ቢቀሩ ጨረታውን ከመክፈትም ሆነ የጨረታውን ሂደት ለሚወስነው ውሳኔዎች ተገዥ ናቸው፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በመጠቀም በተገለጸው ዝርዝር መግለጫ ስፔስፍኬሽን/ መሰረት መሞላት ይኖርበታል። እንዲሁም ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ተለይቶ በዝርዝር በመሙላት የድርጅቱን ስም፣ ቀን፣ በመፃፍ በመፈረምና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጪ ይሆናል ይደረጋል።
- ግንባታው በባለሙያ መታየት ስላለበት ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው በባለሙያ አረጋግጠን የምንረከብ መሆኑን እናሳውቃለን።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ይህ ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልጻለን፤
- የጨረታ መክፈቻው የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 13 40 06 23 መደወል ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን
ባቲ ከተማ አስተዳደር ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ ቤት
