በጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የካርድ ቤት ዕድሳት ለማከናወን የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ BC-6/GC- 6 ከዚያ በላይ ያሉትን የሥራ ተቋራጮች በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የካርድ ቤት ዕድሳት ለማከናወን የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ BC-6/GC- 6 ከዚያ በላይ ያሉትን የሥራ ተቋራጮች በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- ከውዝፍ ግብር ነፃ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያለው፤
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ተጫራቾች ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ የማይመለስ 1000.00 /አንድ ሺህ/ ብር በመክፈል የጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋስትና ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዕድሳቱን የሚያከናውኑበትን ዋጋ ዋናውንና ኮፒ አንድ /1/ እና ካምፓኒ ፕሮፋይል ዋናውንና ኮፒ አንድ /1/ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30-4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ አስገብተው በዚሁ ቀን በ4፡50 ሰዓት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል ጊቢ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 047 151 3042 ይጠቀሙ።
የጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል
