ኢትስዊች አ.ማ የተሽከርካሪ ኪራይ (የሰርቪስ አገልግሎት) ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ድርጅቶችን አወዳድሮ በውድድሩ ብቁ ከሆነው ድርጅት ጋር ለ1 (አንድ) ዓመት የሚቆይ የውል ስምምነት ማድረግ ይፈልጋል።
ETHSWITCH
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ
የተሽከርካሪ ኪራይ (የሰርቪስ አገልግሎት ግዥ)
የጨረታ ቁጥር፡ RE-ETS/NCB/026/2024
ኢትስዊች አ.ማ የተሽከርካሪ ኪራይ (የሰርቪስ አገልግሎት) ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ድርጅቶችን አወዳድሮ በውድድሩ ብቁ ከሆነው ድርጅት ጋር ለ1 (አንድ) ዓመት የሚቆይ የውል ስምምነት ማድረግ ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መካፈል የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።
- በዘርፉ የተሰማሩ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን የቴክኒክ እና የዋጋ ሰነዶቻቸውን ዋና እና ኮፒ አንድ ላይ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ብር ሰላሳ ሸህ) በሲፒኦ ወይም ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመክፈቻው ሰዓት በፊት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ብር ሁለት መቶ) ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ 7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በአስተዳደር መምሪያ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- የቴክኒክ ዋጋ ሰነዱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ በ5፡30 ላይ ኮሜርስ ፊት ለፊት፤ ዘመን ባንክ 20ኛ ፎቅ አስተዳደር መምሪያ ይከፈታል።
- ኢትስዊች አ.ማ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትስዊች አ.ማ
አስተዳደር መምሪያ
ስልክ ቁጥር ፡ +251-11-557-12-04/05
ፋክስ ፡ +251-11-557-11-15
አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ
