በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለድሬዳዋ መልካ ጀብዱ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ለስራ አገልግሎት የሚውል በቁጥር (5) አምስት ዳብልካፕ መኪና መከራየት ይፈልጋል፡፡
የመኪና ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለድሬዳዋ መልካ ጀብዱ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ለስራ አገልግሎት የሚውል በቁጥር (5) አምስት ዳብልካፕ መኪና መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አከራዮች የሚያቀርቡት ፒካፕ መኪና የስሪት ጊዜው ከ2010 ጀምሮ የፈረስ ጉልበት 2500 CC የሆነ ፣
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው/ያላት፣
- የባለቤትነት ሊብሬ የሚያቀርብ፣
- የ3ኛ ወገን መድን ሽፋን የተገባለት፣
- ነዳጅ እንዲሁም የጥገና፣ የሾፌር ደሞዝና አበል በአከራይ ይሸፈናል፡፡
- ለዳብል ካፕ መኪና በቀን የሚከራይበትን ዋጋ ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ከሚገኘው ቢሮአችን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነድ በመውሰድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬዳዋ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ዕለት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች የቴክኒክ ምርመራውን ካለፈ ውል በመፈፀም ወዲያውኑ ወደ ሥራ መሰማራት አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +0251111313/0929063249 /09-67-47-44-90 /09-19-00-80-17 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
