Tender Detail

Tender Details

  • Company CITY GOVERNMENT OF ADDIS ABABA TRADE BUREAU (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ)
  • Address ውቤ በረሃ ደጃች ውቤ 1888 ህንጻ 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118126179
  • Websitehttps://aacatb.gov.et/
  • Deadline06 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Vehicle (Garage Service)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥ አይነት ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


 

መጀመሪያ ጊዜ የጠጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 04/2017

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥ አይነት ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የታሸገ ሚኒራል 1/2 ሊትር ውሃ ግዥ

ሎት 2 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ

ሎት 3 የተሽከርካሪ ጥገና

በዚህ መሰረት ተጫራቾች -

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያለውና 2017 የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ ያላቸው::
  2. ለእቃ አቅራቢነት ስለመመዝገባቸው እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ብር በየሎቱ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ንግድ ቢሮ ስም CPO (ጋራንት ቢድ ቦንድ) በማሰራት ማስያዝ የሚችሉ
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከመጨረሻው ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ ይቆያል::
  5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታከስን ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ቢሮው በሰጣችሁ ፎርማት ላይ በመሙላት እና የድርጅታችሁ ማህተም፣ ፊርማና ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ
    1. ፋይናንሽያል አንድ ኦርጅናል እና ፋይናንሽያል አንድ ኮፒ
    2. ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ቴክኒካል አንድ ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በተለያዩ ፖስታዎች ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
    3. ለሎት 1 ለምትወዳደሩበት ውሃ አንድ (01) ፍሬ ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ -ዓርብ 2:30 -1100 ሰዓት ድረስ የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 803 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸኋል፡፡
  8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ 11ኛው ቀን ማለትም የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወደም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት (ማቅረብ) አይቻልም፡፡
  10. ቢሮው ብዛቱን በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ በገለፅነው መሰረት መቀነስና መጨመር የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118126179/0111703024/ በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል

አድራሻ ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ውቤ በረሃ 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ

 

Save Tender