Tender Detail

Tender Details

  • Company Hailemariam & Roman Foundation (HRF) (ኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን)
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 09-16-83-43-09
  • Websitehttps://www.haileromanfoundation.org/
  • Deadline31 Mar 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-03-31 00:00:00
  • Categories Vehicle

ኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን በደቡብ ኦሞ እና በአሪ ዞን የተለያዩ አርብቶ አደር አካባቢዎች ለሴቶች እና ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎች አገልግሎት የሚውል TOYOTA LAND CRLUSER 4.6 V8 EXR 2020 እና 2023 የሆኑ Mark 2 Hardtop እና TOYOTA HIGHLANDER HYBRID 4WD, 2023/24 Model, Silver Color, ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር :- HRF/SV/001/2015

 

ኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን በደቡብ ኦሞ እና በአሪ ዞን የተለያዩ አርብቶ አደር አካባቢዎች ለሴቶች እና ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎች አገልግሎት የሚውል TOYOTA LAND CRLUSER 4.6 V8 EXR 2020 እና 2023 የሆኑ Mark 2 Hardtop እና TOYOTA HIGHLANDER HYBRID 4WD, 2023/24 Model, Silver Color, ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ 2017 . የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ወይም የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስ ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት በማካተት በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ወደ ሽሮ ሜዳ መሄጃ መንገድ አሜሪካ ኤምባሲ አጠገብ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ህንጻ 3 ፎቅ በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው መጋቢት 22 ቀን 2017 . 400 ይዘጋል፡፡ ጨረታው በጨረታው ፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ መጋቢት 22 ቀን 2017 . 400 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  6. ተጫራቾች ለአገልግሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60 ቀናት ነው፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 30 ቀናት ነው፡፡

ፋውንዴሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ 09-16-83-43-09/ 09-62-18-11-49 ይደውሉ፡፡

 

ኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን

 

Save Tender