በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የኮንስትራክሽን ዕቃዎች /4000.00/፣ የጽህፈት መሳሪያዎች /3000.00/ እና የጽዳት ዕቃዎች /1000.00/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል
1. የኮንስትራክሽን ዕቃዎች /4000.00/
2. የጽህፈት መሳሪያዎች /3000.00/
3. የጽዳት ዕቃዎች /1000.00/
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
በዚሁ መሰረት:-
-
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ማስረጃ ያላቸው።
-
የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 ብር /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ በብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ መ/ቤቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
-
የጨረታ ማስከበሪያውን ሲ.ፒ.ኦ ኦሪጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታው ውስጥ አስገብተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
-
ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመምሪያው ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ19/07/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 03/08/2017 ዓ/ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 8:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ መሆኑንና ጨረታው በዚሁ እለት በ03/08/2017 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 9:00 ሰዓት በማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በተጠቀሱት በየጨረታው አይነት ፊት ለፊት የተገለፀውን የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
-
አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
-
የውድድሩ ሁኔታ በተናጠል በየዘርፉ በነጠላ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
-
የበለጠ መረጃ ካስፈለገዎት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም በስልከ ቁጥር 011 681 17 92 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
-
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሰ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ
