Tender Detail

Tender Details


የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በጀት ለ2ኛ ዙር ለሥልጠና የሚውል የስቴሽነሪ፣ የኤሌክትሪክ/ ኤሌክትሮኒክስ፣ የኮንስትራክሽን፤ የጋርመንት፣ የአውቶሞቲቭ፣ ለሆቴል እና ለውበት ሳሎን ማሠልጠኛ የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 .ም በጀት ለ2ኛ ዙር ለሥልጠና የሚውል የስቴሽነሪ፣ የኤሌክትሪክ/ ኤሌክትሮኒክስ፣ የኮንስትራክሽን፤ የጋርመንት፣ የአውቶሞቲቭ፣ ለሆቴል እና ለውበት ሳሎን ማሠልጠኛ የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፦

  1. በሥራ መስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ወይም ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፣

  3. የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣

  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ቼከ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡

  6. የአንድ ሰነድ ዋጋ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ኮሌጁ ለዚህ ጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: ሳጥኑ 11ኛው ቀን ከቀኑ በ800 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው ዕለት በ900 ሰዓት ይከፈታል፡፡

  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ የቀረበው ዋጋ ቫት ያካተተ እንደሆነ ተቆጥሮ ይወሰዳል፡፡

  8. የሽያጫችሁን ቫት 7.5% እና ዊዝ ሆልድ 2% የሚቆረጥ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡

  9. የጨረታው አሸናፊ በጨረታው ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ ሲታዘዝ ኮሌጅ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብና የዕቃው ጥራት በተጠቃሚ ባለሙያ ሲረጋገጥ ብቻ ርክክብ የሚደረግና ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

  10. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስ.0221115245 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡


አድራሻ ፡- አዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳማ ከተማ ቀበሌ ደደቸ አራራ (04)


በኦሮሚያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ሙያ ቢሮ የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ



 

Save Tender