Tender Detail

Tender Details

  • Company ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • Address ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 ሀይሌ ት/ቤት ጎን ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0582204798
  • Website
  • Deadline21 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-21 00:00:00
  • Categories Cargo Vehicle

ኩባንያችን ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ በ124 ሄክታር ላይ በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አንድ SINO Howo 6 X4 Cargo Chassis 370-450 HP Truck Chassis Tier 12 X 20 1450 × 2350 × 3300 mm የደረቅ ጭነት መኪና ለመግዛት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ኩባንያው ተጫራቾችን ይጋብዛል።


 

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የመኪና ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ኩባንያችን ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ በ124 ሄክታር ላይ በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አንድ SINO Howo 6 X4 Cargo Chassis 370-450 HP Truck Chassis Tier 12 X 20 1450 × 2350 × 3300 mm የደረቅ ጭነት መኪና ለመግዛት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ኩባንያው ተጫራቾችን ይጋብዛል።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነበር/ ያላቸው።

3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣

4. ህጋዊ የመኪና አሰመጪነት ፈቃድ ያላቸው፣

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6. የሚገዙ ንብረቶች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

7. የጨረታ ሰነዱን ብር 100 የማይመለስ በመክፈል ዘወትር ስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 007 በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጋቢት 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን እስከ ሚያዚያ 12/2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በጣና ፍሎራ ኃላ የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በመገኘት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይቻላል።

9. ጨረታው ሚያዚያ 13/2017 ዓ.ም ከቀኑ 3፡30 ታሽጎ ባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/ የግ/ማህበር ቢሮ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚያልቅበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል።

10. ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ CPO፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0928958316/0913696383 ወይም 0582204798 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

12. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።

13. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ድረስ በመቅረብ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።

14. አሸናፊው ንብረቶቹን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት መሆን ይኖርበታል።

15. የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ህጋዊ ማስረጃዎችን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

16. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ: ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 ሀይሌ ት/ቤት ጎን ስልክ ቁጥር 0582204798፣ ኢሜል፡- tanaflorapum@gmail.com, tanafl oragm@gmail.com, tanafloraV@gmail.com

 

ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 

Save Tender