የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት አመት የዞኑ ፖሊስ መምሪያ G+4 ህንፃ ግንባታ ስራ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ደረጃቸው Bc-2/Gc-3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት አመት የዞኑ ፖሊስ መምሪያ G+4 ህንፃ ግንባታ ስራ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ደረጃቸው Bc-2/Gc-3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለ2017 በጀት የንግድ ሥራ ፈቃድ ያሳደሱ፤ በሥራና ከተማ ልማት ሚንስቴር የተመዘገቡ እና የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት 2017 በጀት ዓመት ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላው የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ለአቅራቢነት የተመዘገቡ እና በኦዲተር የተረጋገጠ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ሲገዙ እና በጨረታ መክፈቻ ዕለት ኦሪጅናል ዶክመንታቸውን ለማመሳከሪያነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎችን ከራሳቸው አቅርበው መስራት የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (BID Security) 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) (በጥሬ ገንዘብ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (Unconditional BID BOND) ማስያዣ በኦሪጂናል ቴክኒካል ዶክመንት ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 31 (ሰላሳ አንደኛው) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000038613263 በማስገባት እና የባንክ አድቫይስ ይዘው ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኝ በመቁረጥ ከዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው ደረሰኙን በማሳየት የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ከውድድሩ በፊት የሥራ ሳይቱን በራሱ ወጪ አይቶ የማረጋገጫ ደብዳቤ ከጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና የስራ ቦታውን ፎቶ ግራፍ ማቅረብ አለበት፡፡
- የፋይናንሻል ጨረታ ሰነዱ ተሞልቶ አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፍ ኮፒው በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ኦሪጅናልና ኮፒ ተብሎ እላዩ ላይ ተጽፎበት በሶስቱም ፖስታዎች ላይ ስም፣ አድራሻና የፕሮጀክቱ ስም በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም እንዲሁም የቴክኒካል ሰነዶችን አንድ ኦሪጂናል ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (BID Security) በቴክኒካል ኦሪጅናል ፖስታ ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሁኔታ ታሽጎ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን በታሸገ በአንድ እናት ፖስታ እላዩ ላይ ማህተም፣ አድራሻና ስም ጽፎ በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 32ተኛ (ሰላሳ ሁለተኛው) ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ32ተኛ (ሰላሳ ሁለተኛው) ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓግልም፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-8-81-33-38 ጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ መደወል ይቻላል።
ጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
