Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት
  • Address , Phone: 0111572497
  • Website
  • Deadline29 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-29 00:00:00
  • Categories Spare Parts , Industry And Factory , Used Items

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) ንብረት የሆኑ ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ስክራፕ የሆኑ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) ንብረት የሆኑ ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ስክራፕ የሆኑ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ከማእድን ሚኒስቴር የብረት አቅላጭ መሆናቸው የሚገልጽ የተሰጠ የምስክር ወረቀት እና ዝርዝር ላይ የተመዘገበ መሆን ይኖርበታል፡፡ ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ እና ሃያ በመቶ ያላስያዘ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ 16ኛው ቀን 400 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና /ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  4. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው 7 የስራ ቀናት በኋላ 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለኢኢግልድ ገቢ ሆኖ ኢኢግልድ ሌላ አማራጭ መጠቀም ይችላል፣
  5. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2 30 እስከ 1030 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ (የቀድሞ ጅንአድ መስሪያ ቤት) አራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 2 እና ቃሊቲ ከማሰልጠኛ አደባባይ ወደ ሃና ማርያም በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው ቃሊቲ ሽያጭ ቅርንጫፍ በመሄድ የዕቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡
  6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

አድራሻ ፡- አዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡርሃዲዱን ተሻግሮ ወደ አራት መንታ በሚወስደው መንገድ ጣልያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ /ቤት)

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ፦ በስልክ ቁጥር 011-3-69-26-84 /011-8-69-19-95 በመደወል ወይም በድረገፅ www.mewit.com.et ወይም www.eiide.com.et በመጎብኘት ማግኘት ይችላሉ።

 

 

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ)

 

Save Tender