የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የእቃው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የማቅረቢያ ጊዜ |
|
1 |
ሎት 1 |
ስቲል ኬዚንግ (steel casing) አቅርቦት |
100,000.00 |
ከስቶክ |
|
2 |
ሎት 2 |
ኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች አቅርቦት |
50,000.00 |
45 ቀናት |
|
3 |
ሎት 3 |
Flor standing digital signage |
30,000.00 |
45 ቀናት |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድረ-ገጽ www.tisisat.com ማግኘት ይችላል።
የተጫራቾች መመሪያ
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፍኬት፤ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድረ-ገጽ www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው::
- ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PR-02/2013 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለጸው መሰረት መሆን አለበት፡፡ የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማሳሰቢያ፤ ውድድሩ የሚካሄደው እንደ ኩባንያው ፍላጎች በሎት ወይንም በእያንዳንዷ እቃ ነጠላ ዋጋ በሚሞሉት ዋጋ መሰረት ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥራችን 058-220-48-26 /0583202548/ በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 ይጠቀሙ፡፡
የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
