የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በዋናው መስሪያ ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር፣ የውኃ መስመር፣ የስልክና የዳታ መስመር፣ የሻወርና የመፀዳጃ ቤት መስመሮችን የውስጥ ለውስጥ ዝርጋታ፣ የሻወር፣ የመፀዳጃና የጥበቃ ቤት የግንባታ ስራ እና የመኪና ማጠቢያና የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ የግንባታ ስራዎችን ለማሰራት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት የሚሰሩ ደረጃቸው GC/BC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የህንፃ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ/006/2017
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በዋናው መስሪያ ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር፣ የውኃ መስመር፣ የስልክና የዳታ መስመር፣ የሻወርና የመፀዳጃ ቤት መስመሮችን የውስጥ ለውስጥ ዝርጋታ፣ የሻወር፣ የመፀዳጃና የጥበቃ ቤት የግንባታ ስራ እና የመኪና ማጠቢያና የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ የግንባታ ስራዎችን ለማሰራት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት የሚሰሩ ደረጃቸው GC/BC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የህንፃ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ስራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) መክፈልና በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማሲያዝ ያለባቸው ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /Irrevocable or Unconditional Bank Guarantee from Recognized Bank of Ethiopia/ ማስያዝ አለባቸው::
ተጫራቶች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፁትን የቴክኒካል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋናና አንድ ቅጂ ለየብቻው እንዲሁም የፈይናንሻል ሰነድ የያዘ አንድ ዋናና አንድ ቅጂ ለየብቻው እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለየብቻው በፖስታ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢማድረግ አለባቸው::
ጨረታው ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት