የነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በህንፃው ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ምክንያት ህንፃውን ወደ ነበረበት ለመመለስ ያመች ዘንድ ከቃጠሎ የተረፉ የተለያዩ ዓይነት ብረቶች እና አልሙኒየም በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የብረታ ብረት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በህንፃው ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ምክንያት ህንፃውን ወደ ነበረበት ለመመለስ ያመች ዘንድ ከቃጠሎ የተረፉ የተለያዩ ዓይነት ብረቶች እና አልሙኒየም በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በሂሳብ ቁጥር 1000184750507 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ የገቢ ደረሰኝ በመያዝ ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር ሕንፃ ላይ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው ጊዜያዊ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ)
ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
ተጫራቾች የተለያዩ ዓይነት ብረቶችን እና አልሙኒየሞችን የሚገዙበትን የአንድ ኪሎ ግራም የመግዥያ ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ በማሸግ ስምና ፊርማ በማድረግ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊው ተጫራች ውድድሩን ማሸነፉን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ከፍሎ ካለበት ቦታ በራሱ የሰው ሃይል እና ትራንስፖርት አጠቃሎ ማንሳት ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በቅድሚያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአክሲዮን ማህበሩ ገቢ ይደረጋል፡፡ ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ካሉት ተከታታይ ቀናት በ7ኛው የስራ ቀን (Working Days) ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ማሳሰቢያ - ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 7ኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ:- መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-246312 ወይም 0945-986845 መደወል ትችላላችሁ፡፡
ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር
