የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች ፈርኒቸር እና ሞተር ሳይክል ግዥ ለመፈፀም ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱ ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- ወዞፋ/ግ/04/17
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች ፈርኒቸር እና ሞተር ሳይክል ግዥ ለመፈፀም ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱ ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የግዥ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት 1 |
ፈርኒቸር |
50,000.000 ብር |
|
ሎት 2 |
የሞተር ሳይክል |
50,000.00 ብር |
|
ሎት 3 |
የቴክኒክና ሙያ የሥልጠና ግብዓት ዕቃዎች |
50,000.00 ብር |
|
ሎት 4 |
የተለያዩ ሥራ ሥር እና ፍራፍሬ ችግኞች |
50,000.00 ብር |
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት፤ የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፈቃድ ኮፒ እና የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ እየከፈሉ ከወላይታ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ 2ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከኦሪጅናል የጨረታ ሀሳብ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ወይም አገልግሎት ዋጋ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው ዋጋ መሙያ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በጨረታ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 19 መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና 1 የኦሪጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይውሎ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የመንግሥት ገቢ ቫት 7.5% እና 2% Withholding በቅድሚያ የሚሰበስብ መሆኑን ጭምር እናሳስባለን፡፡
- አሸናፊ ድርጅት አስፈላጊውን ውለታ በመፈጸም ዕቃውን /አገልግሎቱን/ ሙሉ በሙሉ ወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ድረስ በማቅረብ ገቢ ሲያደርግ /ሲጨርስ/ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-5-51-21-16 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
