Tender Detail

Tender Details


መ/ቤታችን የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን በእድሳት ምክንያት ንቃይ የእንጨት በሮች ፣ የእንጨት ፓርቲሽን (አካፋይ) የመፀዳጃ ቤት መቀመጫዎች፤ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮች፤ የአሉሙኒየም በሮች፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች ሼልፎች፣ የወለል አምነበረድ፤ ሶፋ ፤ እና የመሳሰሉትን ለሽያጭ በጨረታ ያቀረበ ስለሆነ ከዚህ በታች የተመለከቱን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

/ቤታችን የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን በእድሳት ምክንያት ንቃይ የእንጨት በሮች ፣ የእንጨት ፓርቲሽን (አካፋይ) የመፀዳጃ ቤት መቀመጫዎች፤ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮች፤ የአሉሙኒየም በሮች፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች ሼልፎች፣ የወለል አምነበረድ፤ ሶፋ እና የመሳሰሉትን ለሽያጭ በጨረታ ያቀረበ ስለሆነ ከዚህ በታች የተመለከቱን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  3. የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  4. የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፧
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) Audit service Corporation ስም በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ብር 50 (ሃምሳ ብር) የማይመለስ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 710 በመቅረብ በኮርፖሬሽኑ የሥራ ቀን እና ሰዓት (ቅዳሜ እና እሁድን ሳይጨምር) ጠዋቱ 230 እስከ 630 ከሰዓት በኋላ 800 እስከ 1100 ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍት ሆኖ የሚቆይ እና ጨረታው 11 ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ላይ በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመቀበልም ሆነ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው:
  9. ተጫራቾች በአካል በመቅረብ የሚሸጠውን ንብረቶች በመመልከት የጨረታ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ አድራሻ ቂርቆስ ከፍለ ከተማ ካዛንችስ ከኦዳ ህንፃ (ሲንቄ ባንክ) ፊት ለፊት ወይም ከአይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0913 60 10 06 ወይም 0913 16 65 04 መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን

 

Save Tender