Tender Detail

Tender Details

  • Company Zemen Insurance S.C (ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 251116151493
  • Websitehttps://zemeninsurance.com
  • Deadline06 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-05-06 00:00:00
  • Categories Vehicle , Vehicle Battery

ኩባንያዉ ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸዉን ተሽከርካሪዎችና የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎችን ቅሪቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል::


ዘመን ኢንሹራንስ አክስዮን ማህበር

 

    የጨረታ ማስታወቂያ     .

ቁጥር (003/2017)

 

ኩባንያዉ የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸዉን ተሽከርካሪዎችና የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎችን ቅሪቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹን እና የተሽከርካሪ ቅሪት እንዲሁም ሌሎች ቅሪቶችን ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ቦሌ ኃይሌ እና ዓለም ህንፃ ሁለተኛ ወለል ከሚገኘዉ የኩባንያው ዋናዉ መስሪያ ቤት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመግዛት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሽዋ ዳቦ ወደ ቀኝ ገባ ብሎ በሚገኘዉ የኩባንያዉን የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ (Recovery) ዉስጥ በማየት ሚያዝያ 20 ቀን 2017 . እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 200-600 እንዲሁም ከሰዓት 700 - 1100 ድረስ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።

  1. ጨረታዉ አርብ ሚያዝያ 28 ቀን 2017 . ከቀኑ 730 ተዘግቶ በኩባንያዉ ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዕለቱ አርብ ሚያዝያ 28 ቀን 2017 . ከቀኑ 800 ላይ ይከፈታል::
  2. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም::
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የመነሻ ዋጋዉን 15% (አሥራ አምስት በመቶ) በዘመን ኢንሹራንስ ኩባንያ . ወይም (Zemen Insurance S.C ) ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ከተሽከርካሪ ውጭ ለሆኑ ለተሽከርካሪ ቅሪት እና ሌሎች ቅሪት አካላት ከብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ማነስ የለበትም::
  4. ከቀረጥ ነፃ ከሆኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላት ከጨረታዉ በፊት ዕዳ ቢኖር በኩባንያዉ ይሸፈናል:: በጨረታዉ ለተካተቱት ንብረቶች ከጨረታዉ በኋላ ያሉትን ማንኛዉንም ወጪዎች ገዢው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል::
  5. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት::
  6. የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (Vat )15% (አሥራ አምስት በመቶ) ይሸፍናሉ::
  7. አሸናፊዎች የጨረታዉ ዉጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ውስጥ ክፍያ ፈፅመዉ ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ዉጤት የሚሰርዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባያንዉ ገቢ ይደረጋል::
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹንም ሆነ ሌሎች እቃዎችን ከሪከቨሪ በራሳቸዉ ወጪ ሳይነጣጥሉ በአንድ ጊዜ ከፍለዉ 10 ቀናት ውስጥ ንብረቶቹን ከሪከቨሪ መረከብ ይኖርባቸዋል። በ10 ቀን ውስጥ ንብረቶችን ያላወጣ ተጫራች በየቀኑ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ኪራይ የሚከፍል ይሆናል::
  9. የጨረታ አሸናፊዎች የስም ዝውውር እስከ ስድስት ወር ድረስ ማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ለሚፈጠረው ችግር ኩባንያዉ ኃላፊነት አይወስድም::
  10. ኩባንያዉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነዉ::

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ

ስልክ:- /09-88-80-34-43 /09-44-17-36-73 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::

ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ

አዲስ አበባ

 

Save Tender